በኦሮሚያ ክልል አርሲ ውስጥ በሽርካ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት የተጠረጠሩ
“የፋኖ አባላት እና የኦነግ ሸኔ አባላትን”
ጨምሮ 73 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ተናገሩ። ኃላፊው መግለጫውን የሰጡት አሜሪካ፤ በንጹኃን ዜጎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎች እንዲመረመሩ እና የወንጀሉ ፈጻሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡከጠየቀች ከሁለት ቀናት በኋላ ነው። በአዲሱ የኦሮሚያ ክልል የዞን አወቃቀር ደቡብ ምሥራቅ ዞን ሽርካ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በወረዳው ቢርቦ እና ጮሌ ቀበሌ ከተገደሉ ሰዎች በተጨማሪ ከ20 በላይ ነዋሪዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በሽርካ ወረዳ ከደረሰው ጥቃት ቀደም ብሎ አጎራባች በሆነው መርቲ ወረዳ ጎራ ሲሊንጎ ቀበሌ ተመሳሳይ ጥቃት ተፈጽሞ ከ15 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው ምንጮች ለቢቢሲ መናገራቸውይታወሳል። የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በበኩሏ በሁለቱ ወረዳዎች በተፈጸመውጥቃት 60 ምዕመኖቿ እንደተገደሉአስታውቃለች። ይህን ጥቃት አስመልክቶ ከሳምንት በፊት መግለጫ የሰጡት የአሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽንአገልግሎት ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ “የፅምዶ አባላትን” ተጠያቂ አድርገው ነበር። ኃላፊው ዛሬ ጥቅምት 23/2019 ዓ. ም. በድጋሚ በሰጡት መግለጫቸው ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 73 ሰዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አሳውቀዋል። በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች የፋኖ እና መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለው ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን አባላት መሆናቸውንም ተናግረዋል። “እነዚህ
73 ሰዎች አንደኛ የጽንፈኛውፋኖ አባላት በዚያ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሽብርተኛውሸኔ አባላቶች ናቸው። እነዚህ ሁለት ኃይሎች ተናብበው ነው የሚሠሩት” በማለት ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት “ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ከማዋል በተጨማሪ”
እየወሰደ ስላለው እርምጃ የተናገሩት አቶ ኃይሉ፤ በኦሮሚያ ክልል “የፅምዶ ኃይሎች እንቅስቃሴየሚያደርጉባቸውን 6 ቀበሌዎችንየማጽዳት ሥራዎች እየተከናወነ ይገኛል” ሲሉ በዛሬው መግለጫቸው ገልጸዋል። የክልሉ መንግሥት ጥቃቱን አስመልክቶ በቁጥጥር ሥር ስለዋሉ ተጠርጣሪዎችያሳወቀው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ፣ በአርሲ ጥቃት የፈጸሙ ለፍትሕ እንዲያቀርቡ ጥሪ ካቀረበ በኋላ ነው። ቢሮው ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት
21/2019 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ አሜሪካ ሃይማኖት እና ብሔርን መሠረት ያደርጉ ጥቃቶችን እንደምታወግዝ አስታውቋል። በኦሮሚያ ክልል ሽርካ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ "ከ40 በላይ ሰዎች" መገደላቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ አሜሪካ በአርሲ የተፈጸሙ ግድያዎች በጽኑ እንዳሳሰቧት ገልጻ በአግባቡ እንዲመረመሩ ጠየቀች




